
Ahadu Radio And Television
June 13, 2025 at 03:33 PM
*ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው ምርት የጥራት ማረጋገጫ ዲጂታል አለመሆኑ ክፍተቶችን እየፈጠረ ነው ተባለ*
ሰኔ 6/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ከውጪ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ምርቶች የጥራት ማረጋገጫ የሚሰጥበት አግባብ ማኑዋል ወይም በወረቀት መሆኑ፤ በኢትዮጵያ የገቢ ምርት ዝውውር ላይ ክፍተቶችን እየፈጠረ ነው ሲል ትሬድ ማርክ አፍሪካ ለአሐዱ አስታውቋል።
በኢትዮጵያ የትሬድ ማርክ አፍሪካ ዳይሬክተር እውነቱ ታየ፤ ማንኛውም የገቢ እና ወጪ ንግድ ጥራቱ ሳይረጋገጥ ወደ የትኛውም ሀገር እንደማይላክና እንደማይገባ ተናግረዋል።
ነገር ግን እስካሁንም ድረስ የጥራት ደረጃው የሚያረጋገጥበት አግባብ በወረቀት ብቻ በመሆኑ እና ወረቀቶች እንደልብ በማይገኙበት ጊዜ ሥራውን በማጓተት የገቢ ምርቱ ላይ ችግር እንዳሳደረበት አንስተዋል።
አክለውም በዓለም ላይ የገቢና ወጪ ንግድ ከሚፈፀምባቸው ከ100 በላይ ሀገራት መካከል የዲጂታል ስርዓቱን ባለመከተል ወደኋላ የቀረችው ኢትዮጵያ እንደሆነች ገልጸዋል።
በዚህም መሠረት ትሬድ ማርክ አፍሪካ የኢትዮጵያን ገቢ እና ወጪ ንግድ ለማጠናከር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ይህንን የምርቶችን የጥራት ደረጃም በዲጂታል ስርዓት እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችሉ ሰፊ ሥራዎች መኖራቸውን ያነሱት ዳይሬክተሩ፤ በቅርቡም ከኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ጋር በመሆን ይፋ የሚደረግ የዲጂታል አሰራር መኖሩን አስታውቀዋል።
በስፍራሽ ደመላሽ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
*ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!*
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
