Ahadu Radio And Television
Ahadu Radio And Television
June 13, 2025 at 03:34 PM
*በደብረ ብርሃን ከተማ ከ5 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች በሰብዓዊ ድጋፍ እጥረት ምክንያት ለችግር መጋለጣቸው ተገለጸ* ሰኔ 6/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በጸጥታ ችግር ምክንያት ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው ከአራት ዓመት በላይ በአማራ ክልል በደብረብረሃን ከተማና በአጓራባች ወረዳዎች የሚኖሩ ከ5 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች በሰብዓዊ አቅርቦት ችግር ምክንያት ለተለያዩ ተላላፊና ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች ተጋላጭ እየሆኑ እንደሚገኙ አሐዱ ያነጋገራቸው ቅሬታ አቅራቢዎች ተናግረዋል፡፡ ምግብ፣ የንጽኅና መጠበቂያና መጠለያ በበቂ ሁኔታ ባለመድረሱ በሕይወታቸው ላይም ስጋት እንደቀነባቸው ገልጸዋል፡፡ ከ16 ከሚደርሱ በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች መፈናቀላቸውን የተናገሩት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፤ "ምንም አይነት ውሳኔ ሳይሰጠን ከአራት ዓመት በላይ በካምፕ ውስጥ እየኖርን ነው" ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡ "በአሁኑ ወቅት የክልሉ መንግሥት ከ800 በላይ ድንኳኖችን በመስራት በአንድ ድንኳን ውስጥ አራት ቤተሰብ እንዲኖር አመቻችቶልን እየኖርን ነው" የሚሉ ተፈናቃዮች፤ "ነገር ግን ክረምቱ ከመቃረቡ ጋር በተያያዘ፤ የምንኖርበት መጠለያ ከዝናብ የሚከላከልም አይደልም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ "የፌደራሉ መንግሥትም ይሁን የክልሉ መንግሥት እንዴት እየኖርን እንዳለን ኢትዮጵያዊን መሆናችንን የዘነጉት ይመስለናል" ሲሉም ቅራታቸውን ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡ "አሁን ቢሆን የሚመለከተው አካል ዜጋ መሆናችንን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ወይ ቀደምት ንብረት ካፈራንበትና መኖሪያ ቀያችን አመቻችቶ መመለስ፤ ይህን ማድረግ ካልቻለ ደግሞ የክልሉ መንግሥት የጸጥታ ስጋት በሌለባቸው አካባቢዎች ጥናት አድርጎ በሰፈራ መልክ እንዲያሰፍረን እንጠይቃለን" ሲሉ አሳስበዋል፡፡ የተፈናቃዮቹን ቅሬታ መነሻ በማድረግ ለተጨማሪ መረጃ ለአማራ ክልል የአደጋና ስጋት አመራር ኮሚሽን ያደረግነዉ የስልክ ሙካራ ሳይሳካ ቀርቷል። ነገር ግን በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሚሰጥ ከሆነ በዘገባ ሽፏን የምንመለስበት ይሆናል። በደረጄ መንግስቱ #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ *ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!* ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
Image from Ahadu Radio And Television: *በደብረ ብርሃን ከተማ ከ5 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች በሰብዓዊ ድጋፍ እጥረት ምክንያት ለችግር መጋለጣቸው ተገለጸ*...

Comments