
Ahadu Radio And Television
June 13, 2025 at 04:57 PM
*በገፈርሳ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ሲደረግ የቆየው ማሻሻያ ሥራ መጠናቀቁ ተገለጸ*
ሰኔ 6/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በመላ ኢትዮጵያ በሚገኙ 75 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ የሚካሄደው የማሻሻያ ሥራ አካል የሆነው የገፈርሳ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ማሻሻያ ሥራ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡
የገፈርሳ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ሲሰራ የነበረውን የማሻሻያ እና አቅም ማሳደግ ሥራ አጠናቆ ጣቢያው በእጥፍ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚያደርገው አቅም ላይ ማድረሱን ነው ተቋሙ የገለጸው።
ከአዲስ አበባ በቅርብ እርቀት ላይ የሚገኘው የገፈርሳ የኃይል ማከፋፈፈያ ጣቢያ የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ እና የታጠቅ ኢንደስትሪ መንደርን ጨምሮ ለሌሎችም እስከ ፊቼ ያሉ አካባቢዎችን የኃይል ተጠቃሚ የሚያደርግ እንደሆነ ተገልጿል።
ነገር ግን ከዚህ በፊት ይነሱበት የነበሩ የኃይል መቆራረጦችን ለመፍታት በተሰራው ሥራ አሁን ላይ እስከ 200 ሜጋ ዋት ኃይል እንዲሸከም ተደርጎ መሻሻሉም ተመላክቷል።
በ230 ኪሎ ቮልት ኃይል ተቀብሎ በ230 ኪሎ ቮልት የሚያስተላልፍ ማከፋፈያን ጨምሮ፤ በ230 የተቀበለውን ኃይል ወደ 15 ኪሎ ቮልት ቀይሮ ለአነስተኛ የኃይል ፍጆታ ተጠቃሚዎች የሚያደርስ ተንቀሳቃሽ ማከፋፈያ መገንባቱን የተቋሙ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ሞገስ መኮንን ለአሐዱ ተናግረዋል።
ተቋሙ አጠቃላይ የአቅም ማሳደግ እና ማስፋፊያ ሥራዎችን በ75 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች እየተሰራ ነው ተብሏል።
በእመቤት ሲሳይ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
*ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!*
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
