Ahadu Radio And Television
Ahadu Radio And Television
June 14, 2025 at 05:03 PM
*ለካንሰር መድኃኒት አቅራቢዎች ተደጋጋሚ ጨረታ ቢወጣም የተሳታፊዎች ብዛት ግን አነስተኛ መሆኑ ተገለጸ* ሰኔ 7/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ሕጉን መሠረት ያደረገ ጨረታ ለካንሰር መድኃኒ አቅራቢዎች በተደጋጋሚ ጊዜ የሚወጣ ቢሆንም፤ ሥራው አዋጭ ባለመሆኑ ምክንያት የመድኃኒት አቅራቢዎቹ በጨረታው ተሳታፊ እንደማይሆኑ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት አስታውቋል። በኢትዮጵያ ለካንሰር በሽታ 54 አይነት መድኃኒቶች እንደሚቀርቡ ለአሐዱ የገለጹት የአገልግሎቱ ዋና ዴይሬክተር አብዱልቃድር ገልገሎ (ዶ/ር)፤ "ከእነዚህም ውስጥ በኢትዮጵያ በተጠናው ጥናት መሠረት አንዳንድ መድኃኒቶች በጣም ውስን ሕመምተኛ ብቻ ያላቸው ናቸው" ብለዋል። በዚህም ምክንያት ሕመምተኞች ለመድኃኒት እጦት እንደሚጋለጡ በመግለጽም፤ ሕመምተኞች እና ምርቱ አነስተኛ ሲሆን ለሥራቸው አዋጭ ባለመሆኑ አገልግሎቱ መድኃኒቶችን የሚረከብ አቅራቢዎችን ለማግኘት እንደሚቸገር አስታውቀዋል። ዳይሬክተሩ አክለውም፤ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ መድኃኒቶችን ከሌሎች ሀገራት ለማስመጣት የሚያስችል መነሻ ሕግ ባለመኖሩ በፍላጎቱ ልክ መድኃኒት ለማስገባት አዳጋች እንደነበረ አንስተዋል። የካንሰር መድኃኒትን በተመለከተ በጤና ተቋማት በኩልም ፍላጎቱ መኖሩን ያነሱት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ነገር ግን ፍላጎቱ ኑሮ በሕጋዊ መንገድ የማይመጣ ከሆነ መድኃኒቱ ለኮንትሮባንድ ወይም ለሕገ-ወጥነት ተጋላጭ መሆኑ እንደማይቀር ተናግረዋል። በመሆኑም እንደ ሀገር አነስተኛ ሕመምተኛ ቢኖር እና አቅራቢ ባይገኝም እንኳ፤ ለየትኛውም ሕመምተኛ መድኃኒት የማቅረብ ግዴታ ሊኖር እንደሚገባ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ባሳለፍነው ሳምንት ሥራ ላይ በዋለው የመድኃኒትና የሕክምና መሳሪያዎች የግዥ አፈፃፀም መመሪያ መሠረት፤ ከሌሎች ሀገራት ጋር ተመሳሳይ መድኃኒቶችን በጋራ ለመግዛትና ለመጠቀም የሚያስችል የጋራ ጥምር ግዢ አሰራር ሕግ መውጣቱን አስታውቀዋል። መመሪያው የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለቱን መሠረታዊ ችግሮች የሚቀረፍ እና ለሀገር ውስጥ አምራቾች ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጥ መሆኑንም አስረድተዋል። ስለዚህም በሕጋዊ መንገድ የተመዘገበ አምራች፣ ደህንነቱ የተረጋገጠ ከሆነና ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች ተለይተው መንግሥት የሚፈለገውን ያህል መድኃኒት ማምጣት ከቻለ፤ በሕገ-ወጥ መንገድ የሚገቡትን የካንሰር እና መሰል መድኃኒቶች በማስቀረት እጥረቱን መቅረፍ እንደሚቻል ተናግረዋል። የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በማዕከል የሚፈፀሙ የመድኃኒት አቅርቦት እና የሕክምና መሳሪያዎች የግዥ አፈፃፀም መመሪያ በቅርቡ ማጽደቁ የሚታወስ ሲሆን፤ በግዥ መመሪያው ላይም በዓለም አቀፍ ግልፅ ጨረታ ግዥ መፈፀም የሚቻልበት የገንዘብ ጣሪያ 3 ቢሊዮን ብር እንዲሆን፣ እንዲሁም የዉስን ጨረታ የገንዘብ ጣሪያ 2 ቢሊየን ብር እንዲሆን መደረጉ ተገልጿል። በስፍራሽ ደመላሽ #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ *ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!* ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
Image from Ahadu Radio And Television: *ለካንሰር መድኃኒት አቅራቢዎች ተደጋጋሚ ጨረታ ቢወጣም የተሳታፊዎች ብዛት ግን አነስተኛ መሆኑ ተገለጸ*   ሰኔ...

Comments