Ahadu Radio And Television
June 14, 2025 at 05:06 PM
*"ሞቢሊቲ ኢ" ከድጋፍ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር በመተባበር 50 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለደንበኞች አስረከበ*
ሰኔ 7/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) "ሞቢሊቲ ኢ" የተሰኘው ድርጅት በእህት ኩባንያው "ድጋፍ ማይክሮ ፋይናንስ" ቆጥበው ሲጠባበቁ ለነበሩና ለብድር ብቁ ለሆኑ ደንበኞቹ በአምስተኛ ዙር 50 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በዛሬው ዕለት አስረክቧል።
ለደንበኞች ተሽከርካሪዎቹ 50 በመቶ ቅድመ ክፍያ በመፈፀም ፤ቀሪውን ከድጋፍ ማይክሮ ፋይናንስ በሚመቻች ብድር በ16 ነጥብ 5 በመቶ ወለድ እንደሚቀርብ ተገልጿል።
በዚህም መሠረት በድጋፍ ማይክሮ ፋይናንስ ቆጥበው ሲጠባበቁ የነበሩና ለብድር ብቁ የሆኑ 50 ደንበኞች የአምስተኛ ዙር የቢ ዋይ ዲ መኪኖችን ተረክበዋል።
በቀጣይም "ሞቢሊቲ ኢ" የተለያዩ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ለደንበኞች ለማቅረብ ዝግጅት ማድረጉን የሲኖ አፍሪካ ትሬዲንግ ዋና ሥራ አስኪያጅ አ/ቶ ሚሊዮን ጌታቸው ለአሐዱ ተናግረዋል።
"ሞቢሊቲ ኢ" በ4 ዓመት የብድር ክፍያ መመለሻ ጊዜ ያቀረበውን ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ልዩ ቅናሽ ሪፌንቲ በሚገኘው ዋና ማሳያው እንዲሁም መስቀል ፍላወር እና ሃዋሳ ፒያሳ ሩት ገበያ በሚገኙት ቅርንጫፎች አመቻችቶ ተጨማሪ ዙር መኪኖችን ለማስረከብ ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ገልጸዋል።
"ሞቢሊቲ ኢ" ከዚህ ቀደም በአራት ዙር
ከቢዋይዲ ሲጉል፣ ቢዋይዲ ኢ 2፣ ቢዋይዲ ዩአን አፕ፣ ቢዋይዲ ዩአን ፕላስ እና ቢዋይዲ ሶንግ ፕላስ ተሽከርካሪዎችን በ50 በመቶ ቅድመ ክፍያ ቀሪውን ከድጋፍ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር በመተባበር ማቅረቡ ይታወሳል።
በአበረ ስሜነህ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
*ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!*
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ