
Ahadu Radio And Television
June 14, 2025 at 05:29 PM
*#አሐዱ_መድረክ*
"በሕወሓት እና በሻዕቢያ መካከል አደገኛ ጥምረት ተፈጥሯል" | "ትላልቅ ዛፎች ተቆርጠው ወደ ኤርትራ ተወስደዋል" አቶ ጠዓመ አራደ
የዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ፓርቲ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዋና ኮሚቴ አባል!
በዚህ ልዩ ቃለ ምልልስ፦
በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ መሠረት፤ ከወር በፊት ምዝገባውን አከናውኖ የፓርቲውን አደረጃጀት፣ ቅርጽ እና አጠቃላይ የትግል ስልቶች በማስተዋወቅ ላይ በሚገኘው "ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ" (ስምረት) ጉዳይ ዙሪያ ከፓርቲው የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዋና ኮሚቴ አባል አቶ ጠዓመ አራደ ጋር ሰፊ ውይይት አድርገናል፡፡
አቶ ጠዓመ ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ በክልሉ በተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ መድኃኒት እና ጤና ተቋማት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ ስለ ጊዜያዊ አስተዳደሩ አሁናዊ እንቅስቃሴ እና ከህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ጋር ስላለው ግንኙነት አንስተናል፡፡
እንዲሁም በትግራይ ክልል አሁናዊ የሰላም ሁኔታ፣ የሰላም ስምምነቱ ያመጣው ለውጥ እና ሙሉ ለሙሉ ተፈጻሚ አለመሆኑ ያስከተለው ጉዳት ላይ በስፋት ተወያይተናል፡፡
በተጨማሪም የኤርትራ መንግሥት በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ከሚመራው የሕወሓት ቡድን ጋር እያደረገው ስለሚገኘው ስምምነት፣ 'የትግራይ ጦር አመራሮች እና የሻዕቢያ ጦር አመራሮች አድርገውታል' ስለተባለው ግንኙነት እና አጠቃላይ በክልሉ እያንዣበቡ በሚገኙ አደጋዎች ዙሪያ ተወያይተናል፡፡
እንዲሁም የቀድሞ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች እና አባላትን በመያዝ የተቋቋመው "ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ" (ስምረት) ፓርቲ፤ የትግል ስልት፣ የርዕዮተ ዓለም ቅርጽ እና ቀጣይ እንቅስቃሴዎች ላይም ከፓርቲው የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዋና ኮሚቴ አባል አቶ ጠዓመ አራደ ጋር በነበረን ቆይታ አንስተናል፡፡
የቆይታችንን (ክፍል አንድ) እንድትከታለሉ በአክብሮት ጋበዝናችሁ!
*ዶ/ር ጠዓመ ከ#አሐዱ_መድረክ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇*
https://youtu.be/7RDX7OpK864?si=9cB5UZO-rA-EPkV5
#አቶ_ጠዓመ_አራደ #ስምረት #ህወሓት #ትግራይ #ኢትዮጵያ #ethiopianpolitics #tigraypolitics #tplf #getachew_reda #debretsion_gebremichael #simretintigray #newparty #abiyahmed #politics #ethiopia #exclusiveinterview #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ