Ahadu Radio And Television
Ahadu Radio And Television
June 15, 2025 at 10:34 AM
*የአውሮፓ ሀገራት በኢትዮጵያ የጤናው ዘርፍ ላይ የሚያደርጉት ድጋፍ ሙሉ በሙሉ መቋረጡ ተገለጸ* ሰኔ 8/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) አሜሪካን ጨምሮ መላው የአውሮፓ ሀገራት ለረጅም ዓመታት በኢትዮጵያ የጤናው ዘርፍ ላይ ሲያደርጉት የነበረውን ድጋፍ ሙሉ ለሙሉ ማቋረጣቸውን፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የድጋፍ አስባባሪ የኢትዮጵያ ተወካይ ዶ/ር አወቀ ጣሳው ለአሐዱ ተናግረዋል። አሜሪካን ጨምሮ መላው የአውሮፓ ሀገራት በድንገት በጤናው ዘርፍ ላይ ሲያደርጉት የነበረውን ድጋፍ ሙሉ ለሙሉ መቋረጡ ችግሩን ይበልጥ ውስብስብ ሊያረገው እንደሚችልም አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ ለረጅም ዓመታት በጤናው ዘርፍ ላይ አንድ ሦስተኛውን ድጋፍ ከለጋሽ ሀገራት ስታገኝ እንደነበር ያስታወሱ ዶ/ር አወቀ፤ "ይህ የድጋፍ መቋረጥ በጤናው ዘርፍ ላይ አሉታዊ ጫና እንደሚያሳድር መንግሥት ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ጥንቃቄ ሊያረግበት ይገባል" ሲሉ አሳስበዋል። እነዚህ ሀገራት ለኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ድጋፍ ለማቋረጥ እንደ ምክንያት ያነሱት፤ የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት እና የምካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ውጥረት ስጋት ደቅኗል በሚል እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ ይህም በዘርፉ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ቀላል እንዳልሆነ አንስተው፤ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ ሀገራት  አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ካናዳ፣ ፊንላንድ፣ ዴንማርክ፣ ሲውዘርላንድና ሌሎችን ጨምሮ እንደነበሩ አስታውሰዋል፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን ድንገተኛ ውሳኔ በትኩረት በማየት የሀገር ውስጥ የፋይናስ ተቋማትን አቅማቸወሰን እንዲያሳድጉ ማበረታት እንደሚጠበቅበት፤ የመንግሥታት ድርጅት የድጋፍ አስተባባሪ የኢትዮጵያ ተወካይ ዶ/ር አወቀ ጣሳዉ ለአሐዱ አስታውቀዋል። በደረጄ መንግስቱ #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ *ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!* ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
Image from Ahadu Radio And Television: *የአውሮፓ ሀገራት በኢትዮጵያ የጤናው ዘርፍ ላይ የሚያደርጉት ድጋፍ ሙሉ በሙሉ መቋረጡ ተገለጸ*   ሰኔ 8/20...

Comments