Ahadu Radio And Television
Ahadu Radio And Television
June 17, 2025 at 09:54 AM
*እስራኤል አዲስ የተሾሙትን የኢራን የጦርነት ጊዜ ዋና አዛዥ መግደሏን አስታወቀች* ሰኔ 10/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት በኢራን አዲስ የተሾሙትን የጦርነት ጊዜ ዋና አዛዥ አሊ ሻድማኒን በቴህራን በአንድ ጀንበር ባደረገው የአየር ድብደባ መግደሉን አስታውቋል፡፡ ይህም ከሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ እስራኤል ኢላማ ያደረገችውን ሁለተኛው የኢራን ከፍተኛ ወታደራዊ አባል ግድያ ነው። ሻድማኒ የተገደሉት በማዕከላዊ ቴህራን በሚገኝ ዋና መሥሪያ ቤት ላይ በተደረገ የአየር ድብደባ ሲሆን፤ "በኢራን ወታደራዊ ተዋረድ ውስጥ ካሉት ከፍተኛ ባለስልጣኖች ውስጥ አንዱን ኢላማ ለማድረግ በመከላከያ ሠራዊት የመረጃ ቅርንጫፍ በደረሰው 'ትክክለኛ መረጃ' መሰረት ነው" ሲል የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት በዛሬው ዕለት በኤክስ ገጹ አስታውቋል፡፡ ሻድማኒ የኢራን ጦር ኃይሎች የአደጋ ጊዜ ትዕዛዝ አዛዥ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፤ በሁለቱም እስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ኮርፖሬሽን (IRGC) እና በኢራን ጦር ውስጥ የመሪነት ሚና ነበራቸው። ሻድማኒ ስልጣኑን የተረከቡት በዚህ ወር መጀመሪያ በእስራኤል ጥቃት የተገደሉትን የካታም አል-አንቢያ ማዕከላዊ ዋና መሥሪያ ቤት አዛዥና የቀድሞው ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሌተናል ጄኔራል አላም አሊ ራሺድ በመተካት ነበር። እንደ እስራኤል መግለጫ ከሆነ፤ ሻድማኒ የኢራንን ወታደራዊ ስትራቴጂ በመቅረጽ ማዕከላዊ ሚና የተጫወቱ ሲሆን፤ "በእስራኤል መንግሥት ላይ ያነጣጠረ የኢራን የጥቃት እቅድ ላይም በቀጥታ ተጽእኖ አሳድረዋል"። የሻድማኒ ኃላፊነቶች "የውጊያ ሥራዎችን መቆጣጠር፣ የሚሳኤል እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ማጽደቅ እና የኢራንን ወታደራዊ ስትራቴጂ በእስራኤል ላይ መቅረጽ ይገኙበታል" ተብሏል። የእስራኤል ጦር “የሻድማኒ መወገድ የኢራን ከፍተኛ ወታደራዊ እዝ ላይ ያነጣጠረው ተከታታይ የጥቃት አካል ነው” ሲልም በመግለጫው አስታውቋል፡፡ የጦርነት ጊዜ ዋና አዛዡ ለኢራንን መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኔይ የቅርብ ሰው እንደነበሩም የተገለጸ ሲሆን፤ ኢራን የአዛዡን ሞት አስመልክቶ እስካሁን ምንም አይነት ማረጋገጫ አልሰጠችም። በእዮብ ውብነህ #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ *ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!* ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
Image from Ahadu Radio And Television: *እስራኤል አዲስ የተሾሙትን የኢራን የጦርነት ጊዜ ዋና አዛዥ መግደሏን አስታወቀች*   ሰኔ 10/2017 (አሐዱ...

Comments