
Ahadu Radio And Television
June 18, 2025 at 06:38 AM
*ኢትዮጵያ የትራምፕ አስተዳደርን የዲፕሎማሲ አካሄድ በትኩረት ልታጤነው እንደሚገባ ተገለጸ*
ሰኔ 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተለያዩ ጊዜያት የሚከተሏቸውን የዲፕሎማሲ አካሄዶች፤ ኢትዮጵያ በትኩረት ልታጤናቸው እንደሚገባ አሐዱ ያነጋገራቸው ባለሙያዎች ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በተያዘው ሳምንት መጀመሪያ ላይ "ኢትዮጵያንና ግብፅን ማደራደር ጦርነቱንም ማስቆም ችያለሁ" ማለታቸው ተከትሎ፤ አሐዱ የፕሬዝዳንቱ ንግግር አንደምታ እንዴት ይታያል? ሲል ባለሙያዎችን አነጋግሯል፡፡
የቀድሞ ዲፕሎማት ዳያሞ ዳሌ፤ "የትራምፕ አስተዳደር ፖሊሲ ከሌሎች የአሜሪካ መንግሥታት ለየት የሚያደርገው የሰጥቶ መቀበል ወይም ጥቅም ላይ የተመሠረተ በመሆኑ ነው" ብለዋል።
በመሆኑም የኢትዮጵያ የዲፖሎማሲ አካሄድ ንግድ ተኮር መሆን እንዳለበት አንስተው፤ "በፖለቲካ እይታ ውስጥ ቋሚ ጠላትም ሆነ ቋሚ ወዳጅ ባለመኖሩ እና የትራምፕ አስተዳደር በፍጥነት የሚቀያየር ፖሊሲ በመከተሉ ትኩረት የሚሻ ነው" ብለዋል፡፡
ሌላኛው አሐዱ ያነጋገራቸው የዓለም አቀፍ እና የፖለቲካ ሳይንስ መምህሩ ደጉ አስረስ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ አሜሪካ በምካከለኛው ምስራቅ ቀጠና ያለውን ጥቅም ለማስጠበቅ ስትል ለግብፅና ለእስራኤል ያላት ትኩረት የጎላ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
"የትራምፖ አስተዳደር በተለየ መልኩ ከጥቅም ጋር የተሳሰረ ነው" ሲሉ ቀደም ብሎ የተነሳውን ሀሳብ የሚጋሩት ዶክተር ደጉ፤ 'የሚደረገው እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ ላይ ጫና ሊያሳድር ይችላል' የሚል ግምት እንደሌላቸው አንስተዋል፡፡
ኢትዮጵ ከአሜሪካ ጋርም ሆነ ከሌሎች የምዕራብና የምስራቅ አውሮፓ ሀገራት ጋር ያላትን የዲፖሎማሲ አቅም በማጠናከር ጥቅሟንና መብቷን እንደ ቀደምቱ ማስቀጠል አለባት ሲሉም ምሁራኖቹ አሳስበዋል።
አሁን የዓለም የዲፖሎማሲ ስርዓት ንግድ ላይ ያተኮረ ስለመሆኑ አንስተው፤ "ኢትዮጵያም ወደ ዉጭ የምትልካቸዉን ምርቶቿን ተደራሽነት ማስፋት ይጠበቅባታል" ሲሉ ጠቁመዋል፡፡
የትራምፕ አስተዳደርን የዲፕሎማሲ አካሄድ ኢትዮጵያ በትኩረት ልታጤነው ይገባል በማለትም፤ አሐዱ ያነጋገራቸው ምሁራን ጠቁመዋል፡፡
ምስል፦ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የበለፀገ
በደረጄ መንግስቱ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
*ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!*
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
