
Ahadu Radio And Television
June 18, 2025 at 12:21 PM
*አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በነጩ ቤተ-መንግሥት ተገናኝተው ተወያዩ*
ሰኔ 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ጄ ትራምፕ ጋር በነጩ ቤተ-መንግሥት ተገናኝተው ተወያይተዋል።
አምባሳደር ብናልፍ ነጩ ቤተ-መንግሥት ሲደርሱ በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ግንኙነት የሚያንጸባርቅ ዲፕሎማሲያዊ አቀባበል እንደተደረገላቸው የኢቢሲ ዘገባ አመላክቷል።
ይህ የመጀመሪያ ግንኙነት በቀጣይ ጊዜያት ለሚደረጉ በርካታ ውይይቶች መጠናከር ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል የተባለም ሲሆን፤ አምባሳደሩ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ተገናኝተው ስላደረጉት ውይይት በይፋ የተገለጸ ነገር የለም
ኢትዮጵያና አሜሪካ ከ120 ዓመታት በላይ የዘለቀ ጠንካራ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፤ በሁለቱ አገራት መካከል እንደ ሰላም፣ ጸጥታና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ጠንካራ አጋርነት ከመፍጠር አንጻር ያሉ ዕድሎችም ሰፊ መሆኑ ተመላክቷል።
አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም በውይይቱ ወቅት የተገኙትን ስቴት ሴክሬተሪ ማርኮ ሩቢዮ ጋርም መገናኘታቸው ተነግሯል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
*ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!*
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
