Ahadu Radio And Television
Ahadu Radio And Television
June 18, 2025 at 12:26 PM
*የኤርታሌ እሳተ ገሞራ እና የሶፍ ዑመር ዋሻን ጨምሮ ሌሎችንም ተፈጥሯዊ መስህቦች በ'ጂኦ ቱሪዝም' መስክ በዩኔስኮ ለማስመዝገብ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ* ሰኔ 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ተቋም /ዩኔስኮ/ ከሚመዘግባቸው የሚጨበጡ እና የማይጨበጡ ቅርሶች በተጨማሪ በ‘ጂኦ ፓርክ’ እና በ‘ጂኦ ቱሪዝም’ ዘርፍ ምዝገባዎች ማካሄድ መጀመሩን ተከትሎ፤ የኤርታሌን እሳተ ገሞራ እና የሶፍ ዑመር ዋሻን ጨምሮ ሌሎችንም ተፈጥሯዊ መስህቦች ‘በጂኦ ቱሪዝም መስክ’ በዩኔስኮ ለማስመዝገብ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ገልጿል። እስከ አሁን በዓለም 560 ሀገራት 229 የጂኦ ፓርኮችን ያስመዘገቡ ሲሆን፤ በአፍሪካ የጂኦ ፓርክ ቅርሶችን ያስመዘገቡ ሀገራት 2 ብቻ መሆናቸው ታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን የሰነድ ዝግጅት እና የዓለም አቀፍ ቅርስ ባለሙያ ተስፋዬ አራጌ፤ ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት ያስመዘገበቻቸው 12 የሚዳሰሱ፣ 6 የማይዳሰሱ ቅርሶች እንዳሏት አስታውሰው፤ "በጆኦ ፓርክ እና በባህላዊ እና ተፈጥሯዊ ቅርስነት ልታስመዘግባቸው የምትችላቸው በርካታ ቅርሶች አሏት" ብለዋል። በዚህም መሠረት በኢትዮጵያ ከሚገኙ ቅርሶች መካከል በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን የሚገኘውን ሶፍ ዑመር ዋሻ በ'ጆኦ ፓርክ' ለማስመዘገብ የሚያስችል ሰነድ በመዘጋጀት ላይ መሆኑን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡ በአፋር ክልል የሚገኘውን የኤርታሌ እሳተ ገሞራን ለማስመዝገብም ተመሳሳይ የሰነድ ዝግጅት ሥራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ በዩኔስኮ በጂኦ ቱሪዝም መስክ ልታስመዘግባቸው ከምትችላቸው ሐብቶች መካከል ሶፍ ዑመር ዋሻ፣ ገርአልታ፣ ኮንሶ፣ አፋር፣ ባሌ ተራሮችና የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርኮች ይገኙበታል። በህይወቴ ጌትነት #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ *ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!* ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
Image from Ahadu Radio And Television: *የኤርታሌ እሳተ ገሞራ እና የሶፍ ዑመር ዋሻን ጨምሮ ሌሎችንም ተፈጥሯዊ መስህቦች በ'ጂኦ ቱሪዝም' መስክ በዩኔ...

Comments