Ahadu Radio And Television
Ahadu Radio And Television
June 19, 2025 at 04:07 PM
*ከ16 ሀገራት የተውጣጡ ከ156 በላይ አቅራቢዎች የሚሳተፉበት 7ተኛው ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት በአዲስ አበባ ተጀመረ* ሰኔ 12/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) 7ተኛው የ"አግሮ ፉድ እና ፕላስ ትፕሪንት ፓክ ኢትዮጵያ" አውደ ርዕይ ዓለም አቀፍ የግብርና የምግብና መጠጥ ግብአቶች፣ የቴክኖሎጂ የፕላስቲክ ህትመትና የማሸጊያ ቴክኖሎጂና ምርቶች ዓመታዊ የንግድ ትርዒት በዛሬው ዕለት በሚሊኒየም አዳራሽ ተጀምሯል። አውደ ርዕዩ ከዛሬ ሰኔ 12 እስከ 14 2017 ዓ.ም ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ኤክስፖዎችንና ኤግዚቢሽኖችን በማዘጋጀት የሚታወቀው ፕራና ኤቨንትስ፣ በአፍሪካና በመካከለኛው ምስራቅ ለረዥም ጊዜ ግንባር ቀደም ከሆኑ የግብርና ምግብ (agrofood) እና ፕላስትፕሪንትፓክ ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒቶች አዘጋጅ የሆነው የጀርመኑ "ፌር ትሬድ መሴ" በጋራ በመሆን ተዘጋጅቷል። በዛሬው ዕለት በተካሄደው የመክፈቻ ሥነ-ስርዓት ላይ የጀርመኑ ፌርትሬድ ዋና ሥራ አስፈፃሚን ጨምሮ አምባሳደሮችና የዲፕሎማቲክ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል። የፌር ትሬድ ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት ፓል ማርዝ በርካታ አቅራቢዎች በንግድ ትርዒቱ ላይ ሥራቸውን እንደሚያቀርቡ ገልጸው፤ ይህም ለኢትዮጵያ ጥሩ ዕድል እንዳለው ተናግረዋል። የፕራና ኤቨንትስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት ነብዩ ለማ በበኩላቸው፤ ለሦስት ቀናት በሚቆየው አውደ ርዕይ ኢትዮጵያ ያላትን ምርት ለማስተዋወቅ እንደሚጠቅማት ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የብራዚል አምባሳደር የሆኑት ጃንዲር ፌሬራ ዶስ ሳንቶስ እና የቱርክ አምባሳደር ባርክ ባራን በሥነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ የንግድ ትርዒቱ የሀገራቱን የኢኮኖሚ ግንኙነት የበለጠ እንደሚያሳድግ አንስተዋል። ምርትን ከማስተዋወቅና ልምድ ከመቅሰም በተጨማሪ ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራርን ለማዳበር እንደሚያስችል የገለጹት ደግሞ፤ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ዴኤታ ሀሰን ሙሀመድ ናቸው። በዚህ አውደ ርዕይ ላይ ከ16 ሀገራት ማለትም ኢትዮጵያን ጨምሮ ከኦስትሪያ፣ ቻይና፣ ዴንማርክ፣ ብራዚል፣ ጀርመን፣ ህንድ፣ ጣሊያን፣ ጅቡቲ፣ ጆርዳን፣ ኬንያ፣ ፖላንድ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ታይዋን፣ ቱርክ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የተውጣጡ ከ156 በላይ አቅራቢዎች ለኢትዮጵያ ገበያ ተብለው የተዘጋጁ ምርቶችን እና አገልግሎታቸውን ያቀርባሉ ተብሏል። በስፍራሽ ደመላሽ #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ *ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!* ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
Image from Ahadu Radio And Television: *ከ16 ሀገራት የተውጣጡ ከ156 በላይ አቅራቢዎች የሚሳተፉበት 7ተኛው ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት በአዲስ አበ...

Comments