Ahadu Radio And Television
Ahadu Radio And Television
June 20, 2025 at 10:14 AM
*በትግራይ የበጀት ዕጥረት ጉዳይ ካልተስተካከለ በቀጣይ ዓመትም አዲሱን ስርዓተ ትምህርት እንደማይጀመር ተገለጸ* 👉 *በክልሉ ሁሉም ተማሪዎች በቀጣይ የትምርት ዘመን ያለ ምንም ክፍያ እንዲመዘገቡ መወሰኑ ተነግሯል* ሰኔ 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በሀገር አቀፍ ደረጃ በ2015 ዓ.ም ተግባራዊ የተደረገው አዲሱ ስርዓተ ትምህርት የበጀት ዕጥረት ጉዳይ ካልተስተካከለ በቀር በቀጣይ ዓመትም በትግራይ ክልል እንደማይጀመር የክልሉ ትምርት ቢሮ አስታውቋል፡፡ በክልሉ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም፤ በአሁኑ ሰዓት በበጀት እጥረት ምክንያት መቋረጡን የቢሮው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ስዩም ሃጎስ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡ አዲሱን ስርዓተ ትምህርት ተግባራዊ ለማድረግ በክልሉ አቅም የሚፈታ እንዳልሆነ የገለጹም ሲሆን፤ ለቀጣይ ችግሩ ካልተፈታ በትምህርት ስርዓቱ ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር አብራርተዋል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ተግባራዊ ለማድረግ እየሰሩ የነበሩ ሥራዎች ከቅርብ ጊዜ ወደህ በፋይናንስ እጥርት ምክንያት ማቋረጣቸውን የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ በተለይ አዲሱን ስርዐዓተ ትምህርት ተግባራዊ ለማድረግ መጽሐፍት ማሳተም፣ ለመምህራን ስልጠና መስጠት እና ተያያዥ ጉዳዮችን ለማከናወን ችግር ማጋጠሙን ገልጸዋል፡፡ "በትግራይ ክልል ያለው የትምህርት ስርዓት በጦርነት እና ክልሉ ላይ ባለው አለመረጋጋት ችግር ምክንያት ድጋፍ የሚያስፈልገው በመሆኑ፤ መንግሥት እና የሚመለከተው አካል ትኩረት ሊሰጠው ይገባል" ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ለቀጣይ የትምርት ዘመን ጥራ ያለው ትምርት ለመስጠጥ እና አዲሱን ስርዓተ የትምርት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ሁኔታዎች ካተመቻቹ፤ ተማሪዎች በነባሩ የትምህርት ስርዓት መማር እንደሚቀጥሉም አብራተዋል፡፡ በአጠቃላይ በሰላም እጦት ምክንያት ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለቀው ሥነ-ልቦናዊ ጫናን ለመቀነስ እና ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ በቀጣይ የትምርት ዘመን ሁሉም ተማሪዎች ያለ ምንም ክፍያ እንዲመዘገቡ በክልሉ ትምርት ቢሮ መወሰኑንም የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ለተለያዩ ልማት እና ለምዝገባ በሚል ተማሪዎች ክፍያ በመክፈል የሚመዘገቡበት ሁኔታ መኖሩን የገለጹም ሲሆን፤ በአሁኑ ሰዓት ያለውን ነባራዊ ሁኔታን በማገናዘብ ያለ ምንም አይነት ክፍያ እንዳይከፍሊ በሚል በክልል ደረጃ ውሳኔ መተላለፉንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡ በትግራይ ክልል በአሁን ሰዓት 416 ትምህርት ቤቶች መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ አለመጀመራቸው የክልሉ ትምርት ቢሮ ያስታወቀ ሲሆን፤ በክልሉ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ላይ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት እየተተገበረ ባለመሆኑ ምክንያት የ6ተኛ ክፍል ተማሪዎች የመልቀቅያ ፈተና እንደማይወስዱ ለአሐዱ መግለጹ ይታወሳል፡፡ በክልሉ አዲሱ ስርዓተ ትምህር ሙሉ ለሙሉ መቼ ይጀመራል የሚለውን ጉዳይ ትምህርት ሚኒስቴር በሚሰጠው ምላሽ የሚወሰን መሆኑንም አስታውቋል፡፡ በአለምነው ሹሙ #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ *ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!* ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
Image from Ahadu Radio And Television: *በትግራይ የበጀት ዕጥረት ጉዳይ ካልተስተካከለ በቀጣይ ዓመትም አዲሱን ስርዓተ ትምህርት እንደማይጀመር ተገለጸ*...

Comments