Ahadu Radio And Television
Ahadu Radio And Television
June 20, 2025 at 10:14 AM
*ከ70 በመቶ በላይ ለወር አበባ የደረሱ ሴቶች የንፅህና መጠበቂያ እንደማያገኙ ተገለጸ* 👉 *ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ 55ሚሊየን የሚደርሱት ሴቶች ናቸው ተብሏል* ሰኔ 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ 35 ሚሊዮን ሴቶች የወር አበባ እንደሚያዩ እና ከእነዚህም መካከል 2 ነጥብ 8 በመቶ የሚሆኑት ብቻ የንፅህና መጠበቂያ እንደሚያገኙ ተገልጿል፡፡ የጤና ሚኒስቴር የማኅበረሰብ ተሳትፎ እና የመጀመሪያ ደረጃ እንክብካቤ መሪ ሥራ አስፈፃሚ እስራኤል አታሮ ለአሐዱ እንደተናገሩት፤ በአገሪቱ በተለይም በገጠር አካባቢዎች የሚገኙ ሴት ተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያ አያገኙም። አክለውም፤ የንጽህና መጠበቂያ ከማያገኙት ሴቶ ተማሪዎች መካከል 36 በመቶዎቹ በትምህርት አቀባበላቸው ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ገልጸዋል። ሴት ተማሪዎች የወር አበባ በሚያዩት ወቅት ከአንድ ቀን እስከ 4 ቀን ከትምህርት ገበታቸው ውጭ እንደሚሆኑ ገልጸው፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከ8 ዓመታቸው ጀምሮ የወር አበባ እንደሚያዩ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ አሉ ተብሎ ከሚገመተው 110 ሚሊየን ዜጎች ውስጥ ወደ 55ሚሊየን የሚደርሱት ሴቶች መሆናቸው በጥናት መመላከቱን የገለጹት መሪ ሥራ አስፈፃሚው፤ ከእነዚህ ውስጥ 35 ሚሊዮን ሴቶች የወር አበባ እንደሚያዩ እዚህም ከ70 በመቶ በላይ የሚሆኑት የንፅህና መጠበቂያ እንደማያገኙ መረጋገጡን ተናግረዋል፡፡ ከውጭ የሚገቡ የንፅህና መጠበቂያ መሳሪያዎች ላይ 30 በመቶ ወደ 10 በመቶ ዝቅ ማድረግ ቢቻልም፤ ከዘርፉ አስፈላጊነት አንፃር በቂ አለመሆኑን እና ነፃ ማድረግ እንደሚገባ አስታውቀዋል። አክለውም እ.ኤ.አ በ2012 የንፅህና መጠበቂያ ዋጋ 17 ብር የነበረ እንደነበር አንስተው፤ በ2024 ደግሞ 79 ብር መድረሱ የገለጹ ሲሆን፤ ለዚህም የዋጋ መጨመር የኑሮ ውድነት፣ ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ የንፅህና መጠበቂያዎች ላይ ታክስ መጣል፣ ግጭት እና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በምክንያትነት እንደሚቀመጡ በጥናቱ መመላከቱን አስታውቀዋል፡፡ "ችግሩን ለመፍታት የግሉ ዘርፍ በስፋት መሳተፍ እንደሚገባ እና በአጋርነት በትብብር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። ሴቶች በወር አበባ ወቅት የሚደርስባቸውን ተፅዕኖ ከፍተኛ በመሆኑን የገለጹት መሪ ሥራ አስፈጻሚው፤ እንደማሳያ በማረሚያ ቤቶች በትምህር ቤቶች ንፅህና የሚጠብቁበት ውሃ እና መፀዳጃ እንደሌለ አስታውቀዋል። በአገሪቱ የሚገኙ የወር አበባ የሚያዩ ሴቶች የንፅህና መጠበቂያ መጠቀም የቻሉት ሴቶች በቀን አንድ ግዜ ብቻ መቀየር እንደሚችሉ የገለጹም ሲሆን፤ "ይህ እንዲሆን ያደረገው የንፅህና መጠበቂያ መሳሪያዎች ውድ በመሆናቸው ነው" ብሏል። የወር አበባ ንፅህና አጠባበቅ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ12ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ8ኛ ጊዜ፤ "ለወር አበባ ንፅህና ተደራሽ የሆነች ሀገርን በጋራ እናረጋግጥ" (Together for a Period Friendly World) በሚል መሪ ቃል ተከብሯል፡፡ በህይወቴ ጌትነት #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ *ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!* ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
Image from Ahadu Radio And Television: *ከ70 በመቶ በላይ ለወር አበባ የደረሱ ሴቶች የንፅህና መጠበቂያ እንደማያገኙ ተገለጸ*   👉 *ከአጠቃላይ የ...

Comments