
Ahadu Radio And Television
June 20, 2025 at 05:27 PM
*"መኖር በጊፍት መንደር" አራተኛው የዓመቱ የሽያጭ ማጠቃለያ ኤክስፖ ተጀመረ*
ሰኔ 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ጊፍት ሪል እስቴት "መኖር በጊፍት መንደር" በሚል መሪ ቃል በመሀል ከተማ ለገሃር ላይ እየገነባ ያለውን ዘመናዊ መንደር ጨምሮ በሌሎቹም ሳይቶቹ የሚገኙ የአፓርትመንት እና የንግድ ሱቆችን ዓመታዊ የሽያጭ ማጠቃለያ ኤክስፖ በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምሯል።
ይህም የዓመቱ አራተኛ የሽያጭ ማጠቃለያ ኤክስፖ ከዛሬ ሰኔ 13 ጀምሮ እስከ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ፤ የጊፍት ሪል እስቴት የሽያጭና ማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ብርቁ ይርጋ አስታውቀዋል።
ድርጅቱ የአፓርትመንት እና የንግድ ሱቆችን ሽያጭ በ2 በመቶ ቅድመ ክፍያ እስከ 25 በመቶ ቅናሽ በማድረግ ማቅረቡን የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ በተጨማሪም 40 በመቶ የባንክ ብድር መመቻቸቱን ተናግረዋል።
ባለፉት 20 ዓመታት በሪል እስቴት ዘርፍ ግንባታዎችን ሲያከናውን የቆየው ሪል ስቴቱ በዓመቱ ባካሄዳቸው ሦስት "መኖር በጊፍት መንደር" የልዩ ቅናሽ ኤክስፖዎች፤ ከ400 በላይ የመኖሪያ ቤቶች እና ሱቆችን ለደንበኞች መሸጡም በኤክስፖው ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ተነግሯል።
ጊፍት ሪል እስቴት በአሁኑ ወቅት በለገሃር፣ በተክለ ሀይማኖት፣ በ22 ማዞሪያ፣ በሲ ኤም ሲ እና በፈረስ ቤት የመኖሪያና የንግድ ቤቶች መንደሮች በመገንባት ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ በመንደሮቹ ትምህርት ቤቶች፣ የሕክምና ተቋማት፣ ሞሎችና የመዝናኛ ስፍራዎች ከበቂ የመኪና ማቆሚያ ስፍራ ጋር ተካቶባቸው እየተገነቡ ስለመሆኑ ተጠቁሟል።
በአበረ ስሜነህ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
*ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!*
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
