Ahadu Radio And Television
Ahadu Radio And Television
June 20, 2025 at 05:28 PM
*በኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግሮች ውስጥ 77 በመቶ የሚሆኑት በግለሰቦች የፖለቲካ አስተሳሰብ ላይ ያነጣጠሩ ናቸው ተባለ* 👉 *ብሔርና ሐይማኖት በተከታይነት እንደሚቀመጡ ተነግሯል* ሰኔ 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ ከሚስተዋሉ የጥላቻ ንግግሮች ውስጥ 77 በመቶ የሚሆኑት የግለሰቦች የፖለቲካ አስተሳሰብ ላይ ሲሆን፤ ብሔርና ሀይማኖት በተከታይነት እንደሚቀመጡ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አስታውቋል፡፡ ባለስልጣኑ በትላትናው ዕለት ባወጣው የአንድ ዓመት የሀሰተኛ ንግግር እና ጥላቻ ንግግር ጥናት፤ የጥላቻ ንግግር በማስተላለፍ ከፍተኛ ቁጥር የሚወስዱት ታዋቂ ሰዎች ናቸው ብሏል፡፡ በጥናቱ ሌሎችም ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው የተመላከተ ቢሆንም፤ 56 በመቶ የሚሆነውን የጥላቻ ንግግር የሚያሰራጩት ግን ታዋቂ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች መሆናቸውን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አማካሪ ታምራት ደጀኔ ተናግረዋል፡፡ የጥላቻ ንግግሩ በዋናነት የሚያተኩረው 77 በመቶ የሚሆነው የግለሰቦች የፖለቲካ አስተሳሰብ ላይ ሲሆን፤ ብሔርና ሀይማኖት በተከታይነት የሚቀመጡም መረጋገጡን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡ በጥናቱ ላይ ሁለተኛ ከፍተኛ ጥላቻ ንግግር ይደርግባቸዋል ተብለው የሚገለጹት ብሔር 15 በመቶ ሲሆን፤ ሐይማኖት ደግሞ 6 በመቶውን እንደሚይዝም መረጋገጡ ተመላክቷል፡፡ ሀሰተኛ መረጃው የተላለፈባቸው መንገዶች ደግሞ በአብዛኛው ሀሰተኛው መረጃው መረጃው የተሰራጨበት አውድ በመጠቀም መሆኑ ሲገልጽ፤ ይህም ማለት የቆየ ድርጊትን አዲስ አድርጎ የማቅረብ አዝማሚያ እንደሚታይም ተገልጿል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አሳሳች መረጃዎች የማቅረብ እና የማይገናኙ ጉዳዮች አገናኝቶ የማቅረብ ሂደቱ በሀሰተኛ መረጃዎች ላይ የሚስተዋሉ ጉዳዮች መካከል መሆኑን ባለልጣኑ አጠናውት ባለው ጥናት ላይ አቅርቧል፡፡ የሀሰተኛ መረጃዎቹ ዓላማማ ማህበራዊ አለመረጋጋት እንዲፈጠረ የመንግሥትን ሥራ ማስተጓጎልና ግለሰቦችን የቡድን ሥም ማጠልሸት ዓላማ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ ደግሞ ዜጎችን ለአደመፅ እና ጥቃት እንዲነሳሱ የማድረግ ሥራ 15 በመቶ የሚይዝ መሆኑ በጥናት የተረጋገጠ ሲሆን፤ የሥም ማጠልሸት ወደ 26 በመቶ የሚደርስ መሆኑን የጥናቱ አቅራቢ ተናግረዋል፡፡ የጥላቻ ንግግር በመግለፅ አካሄድ ከማህበራዊ ሚዲያ በተጨማሪ የመገናኛ ብዘኃን 26 በመቶ ድርሻ ያላቸው መሆኑን የገለጸው ባለስልጣኑ ግለሰቦች ደግሞ 17 በመቶ ድርሻ ይይዛሉ ብሏል፡፡ ጥናቱ በዋናነት የማህበራዊ ሚዲያ ላይ ትኩረት ያደረገ ቢሆንም፤ ከዚህ በመቀጠል የመገናኛ ብዙኃን ላይም ትኩርት የሚያድርግ ጥናት እንደሚደረግም የባለስልጣኑ አማካሪ ታምራት ደጀኔ ተናግረዋል፡፡ የመገናኛ ብዙኃንም ከማህበራዊ ሚዲያ በመቀጠል ከፍተኛ ጥላች ንግግር የሚተላለፍባቸው መሆኑን ባለስልጣኑ ገልጿል፡፡ በአቤል ደጀኔ #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ *ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!* ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
Image from Ahadu Radio And Television: *በኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግሮች ውስጥ 77 በመቶ የሚሆኑት በግለሰቦች የፖለቲካ አስተሳሰብ ላይ ያነጣጠሩ ናቸው ተ...

Comments