Ahadu Radio And Television
Ahadu Radio And Television
June 21, 2025 at 04:43 PM
*#አሐዱ_መድረክ* "ህወሓትን የማዳን ጥረት ባለመሳካቱ ነው 'ስምረት' የተመሠረተው" | "አቶ ጌታቸው ትግራይ ላይ እንደ ከሃዲ (ይሁዳ) እንዲታይ ተደርጓል!" አቶ ጣዕመ አርአዶም የዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ፓርቲ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዋና ኮሚቴ አባል! በዚህ (ክፍል ሁለት) ልዩ ቃለ ምልልስ፦ በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በትግራይ ክልል እያደረገ ስላለው አሁናዊ እንቅስቃሴ እንዲሁም ከክልሉ ጊዜያዊነት አስተዳደር እና ከኤርትራ መንግሥት ጋር እያደረገ ስላለው ግንኙነት በስፋት አንስተናል፡፡ በተጨማሪ የቀድሞው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በቅርቡ ከፌደራሉ መንግሥር ሹመት መቀበላቸውን ተከትሎ፤ ከህወሓት አመራሮች እና ከትግራይ ሕዝብ እየተሰነዘረባቸው ስለሚገኘው ወቀሳም ተወያይተናል፡፡ የኤርትራ መንግሥት ከህወሓት ቡድን ጋር እያደረገ ስለሚገኘው ስምምነት፣ 'የትግራይ ጦር አመራሮች እና የሻዕቢያ ጦር አመራሮች አድርገውታል' ስለተባለው ግንኙነት እና አጠቃላይ በክልሉ እያንዣበቡ ስለሚገኙ አደጋዎችም በስፋት አንስተናል፡፡ በተጨማሪም ከወር በፊት ቅድመ ምዝገባውን አከናውኖ የፓርቲውን አደረጃጀት፣ ቅርጽ እና አጠቃላይ የትግል ስልቶች በማስተዋወቅ ላይ ስለሚገኘው፤ "ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ" (ስምረት) ፓርቲ የትግል ስልት፣ የርዕዮተ ዓለም ቅርጽ እና ቀጣይ እንቅስቃሴዎች ላይ ላይ በስፋት የተወያየን ሲሆን፤ ፓርቲው በመቐለ ከተማ ለማከናወን በዝግጅት ላይ ስለሚገኘው ጠቅላላ ጉባኤም ከፓርቲው የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዋና ኮሚቴ አባል አቶ ጣዕመ አርአዶም ጋር ሰፊ ውይይት አድርገናል፡፡ የቆይታችንን (ክፍል ሁለት) እንድትከታለሉ በአክብሮት ጋበዝናችሁ! አቶ ጣዕመ ከ#አሐዱ_መድረክ ጋር ያደረጉትን ቆይታ (ክፍል ሁለት) ለመከታተል ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👉 https://youtu.be/v9uCH47ODwc?si=cg17aeh111MEGgLU ክፍል አንድን ለመከታተል👉 https://youtu.be/7RDX7OpK864?si=5jolUqIMTBys0Mq- #አቶ_ጣዕመ_አርአዶም #ስምረት #ህወሓት #ትግራይ #ኢትዮጵያ #ethiopianpolitics #tigraypolitics #tplf #getachew_reda #debretsion_gebremichael #simretintigray #newparty #abiyahmed #politics #ethiopia #exclusiveinterview #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

Comments