Ahadu Radio And Television
Ahadu Radio And Television
June 21, 2025 at 05:05 PM
*በአያት ሪል እስቴት በግንባታ ሥራ ላይ የነበሩ ሁለት ሠራተኞች ከአራተኛ ፎቅ ወድቀው ሕይወታቸው አለፈ* 👉 *በተመሳሳይ በትናንትናው ዕለት ሁለት እንዲሁም ከትናንት በስተያ ሁለት ሠራተኞች ከሕንጻው ላይ ወድቀው ሕይወታቸው ማለፋ ተነግሯል* ሰኔ 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በዛሬው ዕለት ከረፋዱ 4 ሰዓት አካባቢ ሲ.ኤም.ሲ ሚካኤል አካባቢ እየተገነባ በሚገኘው አያት ሪል እስቴት ላይ በግንባታ ሥራ ላይ የነበሩ ሁለት ሠራተኞች፤ ከአራተኛ ፎቅ ወድቀው ሕይወት ማለፋን አሐዱ ከቦታው ተገኝቶ ማረጋገጥ ችሏል። አደጋው የደረሰው በልስን ሥራ ላይ ተሠማርተው በነበሩ ሠራተኞች ላይ ሲሆን፤ ሁለት ሠራተኞች ከሕንጻው 4ተኛ ፎቅ ላይ ሆነው የልስን ሥራ በማከናወን ላይ ሳሉ የቆሙበት ሊፍት (ዊንች) ካቦው በመበጠሱ አደጋው ደርሷል። በወቅቱም ከሕንጻው ስር በመጎዝ ላይ የነበረ አንድ ሠራተኛ ዊንቹ ወድቆበት ወዲያውኑ ሕይወቱ ያለፈ ሲሆን፤ ከወደቁት ሁለት ሠራተኞች ውስጥ አንዱ ሠራተኛም በተመሳሳይ ወዲያው ሕይወቱ አልፏል። የልስን ሥራ ሲሰራ የነበረው አንዱ ሠራተኛ ደግሞ፤ ከባድ ጉዳት ደርሶበት ለሕክምና እርዳታ ወደ ሆስፒታል ተወስዷል። በትናትናው ዕለትም 4 የቀን ሥራ ሠራተኞች በተመሳሳይ ሁኔታ ከሪል እስቴቱ ሕንጻ ላይ ወድቀው ሁለት ሠራተኞች ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን፤ በሁለቱ ሠራተኞች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን አሐዱ ያነጋገራቸው የሪል እስቴቱ የግንባታ ሠራተኞች ገልጸዋል። እንዲሁም ከትናንት በስተያ ሐሙስ ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም አምስት የግንባታ ሠራተኞች ከሕንጻው ላይ መውደቃቸው የተገለጸ ሲሆን፤ የሁለቱ ሠራተኞች ሕይወት ሲያልፍ በሦስቱ ሠራተኞች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል ተብሏል። በሕንጻው ግንባታ ላይ የተሰማሩ ሠራተኞች በተደጋጋሚ ተመሳሳይ አደጋ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ አሐዱ የገለጹ ሲሆን፤ በሳምንት አንድ ወይ ሁለት ሠራተኞች አደጋ እንደሚደርስባቸው ተናግረዋል። ሠራተኞቹ አክለውም፤ ሪል እስቴቱ በሠራተኞች ደህንነት ላይ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል። በእዮብ ውብነህ #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ *ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!* ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

Comments