Ahadu Radio And Television
Ahadu Radio And Television
June 21, 2025 at 05:06 PM
*በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በሚተዳደሩ ወረዳዎች ብቻ ከ650 ሺሕ በላይ አካል ጉዳተኞች መኖራቸው ተገለጸ* ሰኔ 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ለአካል ጉዳተኞች የተደነገጉ መብቶችና ጥቅሞች አከባበርን በተመለከተ፤ በትግራይ ክልል በተመረጡ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ላይ ጥናት ማካሄዱን አስታውቋል፡፡ በዚህም በ2016 ዓ.ም በተደረገው የዳሰሳ ጥናት መሠረት በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በሚተዳደሩ ወረዳዎች ብቻ ከ650 ሺሕ በላይ አካል ጉዳተኞች እንደሚገኙ መረጋገጡን፤ የተቋሙ የሕዝብ ግንኙነት እና የኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ አንለይ ወርቄ ለአሐዱ ተናግረዋል። አካል ጉዳተኞቹ በክልሉ የጤናና ሌሎች መሠረታዊ አገልግሎቶች በበቂ ሁኔታ ተደራሽ ባልሆኑባቸው የገጠር አካባቢዎች የሚኖሩ መሆናቸውን የገለጹት ሥራ አስፈፃሚው፤ በተለይም በትግራይ ክልል ተደጋጋሚ ግጭት የነበረበት መሆኑ ቁጥሩ ከፍ ያለ መሆኑን አስረድተዋል። በዚህ መሠረት ተቋሙ በጥናቱ በተለዩ የአሰራርና የሕግ ክፍተቶች መነሻ በማድረግ የመፍትሄ ሀሳብ ያላቸውን እንዲሻሻሉ እና እንዲታረሙ ብሎም፤ ለተለያዩ ጥናቶች ግብዓትነት እንዲውል የመፍትሄ ሃሳብ ማቅረቡን ገልጸዋል፡፡ በዚህም አካል ጉዳተኞችን እና የማህበራዊና ኢኮኖሚያው ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች፤ የማህበራዊ ጥበቃ እንዲደረግላቸው፣ በተለያዩ መሠረታዊ አገልግሎቶች ፍትሃዊ ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ እንዲሁም ለጥቃትንና በደል ተጋላጮች የሕግ ጥበቃና ድጋፍ በአግባቡ ተግባራዊ እንዲደረግ በጥናቱ የመፍትሔ ሃሳብ መቀመጡን ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም የልዩ ፍላጎት ትምህርት በመቐለና ዓዲ-ግራት ብቻ ከሚወሰን ወደ አግልግሎት ላይ እንዲውል፣ የሰው ሃይል፣ በጀትና የቁሳቁስ አቅርቦትን በማሟላት፤ ከባለ ድርሻ አካላት በቅንጅትና በትኩረት እንዲሰራ እንዲሁም፤ የወላጆች የኢኮኖሚ አቅም መሰረት ያደረገ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ቢስፋፉ የሚል መፍትሔ ሃሰብ መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡ ለአካል ጉዳተኞች አስመለክተው የወጡ አዋጆች መመሪያ እና ደንቦችን የተላለፉ አመራር ወይም ፈፃሚ አካላት በሕጉ መሠረት ተመጣጣኝ የሆነ ቅጣት መውሰድ እንደሚገባም በጥናቱ መመላከቱን አስረድተዋል፡፡ የአካል ጉዳተኞችን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶችና ጥቅሞች ለማስከበር ኢትዮጵያ የተቀበለታቸው በርካታ ስምምነቶች፣ ውሎችና ሕጎችን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚያስፈልግም የተቋሙ የሕዝብ ግንኙነት እና የኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ ጠቁመዋል፡፡ ይህ ጨምሮ ሌሎችም የተሰጡ ምክረ ሃሳቦችን ተግባራዊ ማድረግ ከተቻለ አካል ጉዳተኞች በህብረተሰቡ ውስጥ ተካታችና በልማት፣ በፖለቲካና በምጣኔ ሃብት ዘርፍ ተሳታፊ እንዲሆኑ ያስችላል ተብሏል። በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ቁጥራቸው በርከት ያሉ አካል ጉዳተኞች እንደሚገኙ የሚገመት ሲሆን፤ እ.ኤ.አ በ2007 በተካሄደው ብሐራዊ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ መሠረት በአገሪቱ ውስጥ 805 ሺሕ 492 አካል ጉዳተኞች እንደሚኖሩ ስታስቲክሱ ያሳያል፡፡ ከእነዚህም አካል ጉዳተኞች ውስጥ 84 በመቶ የሚሆኑት ለመሰረታዊ አገልግሎት ተደራሽ እንዳልሆኑ ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡ በአበረ ስሜነህ #አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ *ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!* ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
Image from Ahadu Radio And Television: *በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በሚተዳደሩ ወረዳዎች ብቻ ከ650 ሺሕ በላይ አካል ጉዳተኞች መኖራቸው ተገለጸ*  ...

Comments