
Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ
1.8K subscribers
About Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ
አል ዐይን የአማርኛ ዜና ድረ-ገፅ ሲሆን ፖለቲካዊ፡ኢኮኖሚያዊና ስፖርታዊ ዜና በዓለምአቀፍ ደረጃ በተአማኒነት የሚያቀርብ አንዱ የአል ዐይን ሚዲያ ፕላት ፎርም ኔትወርክ ነው፡
Similar Channels
Swipe to see more
Posts

ግንኙነታቸውን ለማደስ የተስማሙት የአሜሪካ እና ሩሲያ ባለስልጣናት ድጋሚ ሊገናኙ ነው ሶስት አመታት ለሚጠጋ ጊዜ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የነበሩት ሀገራት ከአመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው በሚመራ ከፍተኛ ልዑክ ባሳለፍነው ማክሰኞ በሳኡዲ ተገናኝተው መምከራቸው ይታወሳል፡፡ https://is.gd/dnsCwB

እስራኤልን ያስገረመው የያህያ ሲንዋር አስከሬን ምርመራ ውጤት የቀድሞው የሃማስ መሪ ጭንቅላት ውስጥ ያሉ ጥይቶች እንዳይወጡ ተወስኗል። ጥይቶቹ የማይወጡት በምን ምክንያት ነው? የአስከሬን ምርመራ ውጤቱ ግኝት ምን ይመስላል? በተከታዩ ሊንክ ምላሹን ያገኙታል፦ https://tinyurl.com/27wdpyex

ትራምፕ የአሜሪካን ከፍተኛ ወታደራዊ መሪ አባረሩ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በከፍተኛ የፔንታጎን አመራሮች ላይ እየወሰዱት ባለው ያልተጠበቀ እርምጃ የጆይት ቺፍ ኦፍ ስታፍ መሪ የሆኑትን የአየር ኃይል ጀነራል ሲ.ኪው. ብራውንን በትናንትናው እለት አባረዋል። ትራምፕ ትሩዝ በተባለው ማህበራዊ ገጻቸው ከዚህ በፊት የነበሩ አሰራሮችን በመጣስ በጡረታ ተሰናብተው የነበሩትን ሌትናንት ጀነራል ዳን ኬይን የጄነራል ብራውንን ቦታ እንዲተኩ ማጨታቸውን ገልጸዋል። https://is.gd/hRVvgz

በ26ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል በሜዳው ሽንፈት አስተናግዷል። ለዌስትሃም ጃሮድ ቦውን በ44ኛው ደቂቃ ብቸኛዋን የድል ጎል አስቆጥሯል። የሚኬል አሬታ ቡድን ነጥብ መጣሉን ተከትሎ መሪው ሊቨርፑል ከመድፈኞቹ ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት ስምንት ደርሷል። በተጠባቂው የሊጉ መርሃ ግብር ሊቨርፑል ነገ ምሽት 1 ስአት ከ30 ላይ በኢትሃድ ማንቸስተር ሲቲን ይገጥማል። የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ! ዋትሳአፕ፤ https://bit.ly/48Qmefc ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@alainnewsamharic X (ትዊተር): https://x.com/AlainAmharic ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic ድረገፅ: https://am.al-ain.com ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic

አውሮፓ ያለአሜሪካ ድጋፍ ራሱን ከጥቃት መከላከል የሚችልበት አቅም ይኖረው ይሆን? አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ወደ ስልጣን መምጣት እና በውጭ ጉዳይ የሚከተሉት ፖሊሲ ለየት ማለት አህጉሩ ከደህንነት እና ዋስትና ጋር በተገናኘ ራሱን ችሎ ለመቆም በተለያዩ መንገዶች እየመከረ ነው፡፡ https://is.gd/LvfVfh

ሀማስ በመጀመሪያው ዙር የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት የመጨረሻዎቹን ስድስት ታጋቾች ለቀቀ እስራኤልና ሀማስ ዘላቂ ተኩስ አቁም በሚደረግበትና የእስራኤል ጦር ከጋዛ ጠቅልሎ በሚወጣበት ጉዳይ ሁለተኛ ዙር የተኩስ አቁም ድርድር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። https://is.gd/io18ic

የጀርመን ህግ አውጪ ምክር ቤት ምርጫ ዛሬ ተጀምሯል 630 ወንበር ያለው የጀርመን ምክር ቤት ምርጫ ውጤት የሀገሪቱ መራሄ መንግስት ማን ሊሆን እንደሚችል ፍንጭ ይሰጣል ፍሬድሪክ ሜርዝ ለአሸናፊነት በሚጠበቁበት በዚህ ምርጫ የሩሲያ እና ትራምፕ ወዳጅ ናቸው የሚባሉት አሊስ ዋደል ከባድ ተወዳዳሪ ይሆናሉም ተብሏል ተጨማሪ ያንብቡ https://am.al-ain.com/article/germany-election-2025

የአባ ፍራንሲስ የጤና ሁኔታ በአስጊ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ቫቲካን አስታወቀች የአባ ፍራንሲስ የጤና ሁኔታ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ መባባሱን ቫቲካን ትናንት አስታውቃለች። የሮማው ጳጳስ አባ ፍራሲስ በሳምባ ምች ተጠቅተው ሆስፒታል መግባታቸው ይታወቃል። ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3XdHaZK

በሰረቁት ክሬዲት ካርድ ሎተሪ የቆረጡት ሌቦች የ500 ሺህ ዩሮ እጣ እድለኛ ሆኑ የክሬዲት ካርዱ ባለቤት ሌቦቹ ትኬቱን ይዘው የሚቀርቡ ከሆነ ገንዘቡን እንደሚያካፍላቸው ቃል ገብቷል። https://tinyurl.com/26tfnnk8

ሀማስ አቬራ መንግስቱን ጨምሮ ሁለት ታጋቾችን ሲለቅ፣ ተጨማሪ አራት ለመልቀቅ በሂደት ላይ ነው እስራኤል በምትኩ 602 የሚሆኑ ፍልስጤማውያን እስረኞችን ከእስርቤቶቿ ትለቃለች ተብሎ ይጠበቃል https://am.al-ain.com/article/israel-releases-two-hostages-expected-release-four-soon